The Deeper Walk
Elsa and Zelalem
Journey
Book
Presence | Participation | Practice
መገኘት (ሰአት ማክበር) - መሳተፍ (ጸጋን መጠቀም) - መኖር (በተግባር ምስክርነት)
▶ Watch YouTube PLAYLIST መጽሐፍ በድምጽ
▶ Watch YouTube PLAYLIST አገልጋይ
ምእራፍ አንድ
ታናሽ መንጋ ቤተክርስቲያን
1. የታናሽ መንጋ እሴት ምንድነው? ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የጸሎት ግሩፕ በምን ይለያል?
2. የታናሽ መንጋ ጥቅም ምንድነው? ይህን በመተዋችን ምን ቀረብን?
3. ታናሽ መንጋ በሐዋርያት ዘመን ምን ቦታ ነበረው? ይህን ቃል ክርስቶስ መቼና እንዴት ተጠቀመ?
4. ታናሽ መንጋ በዘመናት ውስጥ በስራ ላይ የዋለው በምን ሁኔታ ነው? በኢትዮጵያስ ውስጥ? ይህ የሆነው ለምንድነው?
5. ታናሽ መንጋ አሁን በስራ ላይ የማይውለው ለምንድነው? እንዲታደስ ምን እናድርግ?
ቤተ ክርስቲያን
1. ሁለቱ ቤተክርስቲያናት (የምትታይና የማትታይ) ልዩነት ምንድነው? የሚገጣጠሙበትስ ሁኔታ ምን ይመስላል?
2. በዘመናችን የቤተ ክርስቲያን ቁመና በሁለቱ ቤተክርስቲያናት አውድ እንዴት ይመዘናል?
3. ታናሽ መንጋ ለመላው ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተሀድሶ ሲያመጣ በአንድነት መንፈስ ሊሆን የሚችለው ለምንድነው?
4. ታናሽ እና የተለምዶ ቤትክርስቲያናት መዋቅሮች ያላቸው አስተዋጽዎ ምንድነው? እንዴትስ ይመጋገባል?
5. ታናሽ መንጋን ለራሳችን በረከት እንዲያመጣ በራሳችን እንዴት እናስተናግደው?
ምእራፍ ሁለት
ባለ ራእይ
1. ግለሰቦች ባለ ራእይ ተብለው ለምን ይጠራሉ? ይህስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው? ለምን?
2. ለቤተ ክርስቲያን ባለ ራእዩ ማነው? ይህስ ራእይ ምንድነው? እንዴትስ ያሳውቀናል?
3. ግለሰቦች ባለ ራእይ ሆነው ባሉበት ቤተክርስቲያን ባህሪይ ምን ይስመስላል? አደጋውስ ምንድነው?
4. ክርስቶስ ባለ ራእይ ሆኖ የነገሰበት ቤተክርስቲያን ባህሪይ ምን ይመስላል? በረከቱስ ምንድነው?
5. ራእይ ለቤተ ክርስቲያን ያለው ሚና ምንድነው?
ባለ አደራ
1. ባለ አደራ ማለት ምን ማለት ነው? ከባለ ራእይ ጋር ያለው ቁርኝት ምንድነው?
2. ባለ አደራ ለመሆን ሊኖረን የሚገባው የሕይወት መገለጫዎች ምንድን ናቸው?
3. ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ መሆኑ፤ መሪዎች በቤተ ክርስቲያን ካላቸው ሚና ጋር እንዴት ይጣጣማል?
4. መሪዎች ዋና ጥሪና አደራ ከቅዱሳን አንጻር ምንድነው?
5. የቅዱሳን ዋና ጥሪና አደራ ከመሪዎች አንጻር ምንድነው?
Elsa and Zelalem
Journey
Book